|
![]() |
|||
|
||||
Overview""ፍለጋ"" የተሰኘው ይህ የባለ ሦስት ቅጽ እኔ በእንተእኔ ሁለተኛ ጥራዝ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የየመን ሙዋላዲኖች (በውጭ ሀገራት ተወላጅ የሆኑ የመኖች) ለእኩል መብትና ለዜግነት ፍቃድ ስለሚያደርጉት ትግል ያወሳል። መሃይምነትና ተከታታይ የጎሳ ግጭቶች ልማትንና ዘመናዊነትን በማጨናገፍ፣ አሁንም ሀገሪቱንና አካባቢዋን በማወክ ላይ ናቸው። ወደ ቅድመ አያቶቹ ምድር በተሰደደ አንድ የአሥራ ስድስት ዓመት ልጅ ተጋድሎ ውስጥ፣ የየመንን መሠረታዊ መገለጫዎች ፍንትው አድርገው ለመረዳት ይገድዎታል? እንግዲያውስ ይህ የእርስዎ መጽሐፍ ነው። በምድር ላይ ካሉት ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዱ የነበረውና፣ የአረብ ሥልጣኔ መገኛ የሆነው፣ የንጉስ ሰሎሞን እንግዳ በነበረችው በመጽሐፍ ቅዱሳዊቷ በንግሥተ ሳባ ምድር መጻተኛው ምን ገጠመው? በሰሜን በኩል ከሴማዊ አገሮችና ከቀይ ባህር ማዶ ከአፍሪካ ቀንድ ባህሎች ጋር ግንኙነት ያላት የመን፣ አሁን በጊዜ ተለዋዋጭነት ተክዳ የመካከለኛውን ዘመን ባህሎች የሙጥኝ ብላለች፡፡ ዓድል በየመን በቆየባቸው ጥቂት ዓመታት መገለልን፣ መድሎንና የእርስ በርስ ጦርነትን ገፈት ቀምሷል፡፡ የሚኮራበት ጠይም የምሥራቅ አፍሪካ የቆዳ ቀለሙ ኋላቀርና ጥንታዊ ከሆነው የየመን ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ እንዳይዋሃድ እንቅፋት ሆኖበት ነበር። ዓድል ይህንን ሁሉ መሰናክል አልፎና የአያት ቅድመ አያቱን ምድር ለቆ፣ ወደ ተሻለ ሀገር መሄድ የቻለው ጠንካራ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ አማራጭ ስለሌለውም ጭምር ነበር። Full Product DetailsAuthor: Adel Ben-HarharaPublisher: Adel Ben-Harhara Imprint: Adel Ben-Harhara Dimensions: Width: 12.70cm , Height: 1.70cm , Length: 20.30cm Weight: 0.318kg ISBN: 9781778023347ISBN 10: 1778023347 Pages: 292 Publication Date: 01 January 2024 Audience: General/trade , General Format: Paperback Publisher's Status: Active Availability: Available To Order ![]() We have confirmation that this item is in stock with the supplier. It will be ordered in for you and dispatched immediately. Language: Amharic Table of ContentsReviewsAuthor InformationTab Content 6Author Website:Countries AvailableAll regions |