|
|
|||
|
||||
Overviewከ ሀ እስከ ፐ እና ከ፩ እስከ ፻፼፡ የግዕዝ ፊደሎች እና ቁጥሮች ለጀማሪዎች! በኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ልዩ በሆነው የግዕዝ ፊደላት እና የቁጥር ሥርዓት - ከ ሀ እስከ ፐ እና ከ፩ (አንድ) እስከ ፻፼ (አንድ ሚሊዮን) ድረስ የኢትዮጵያ የጥበብ መጀመሪያ ጉዞዎን ከኛ ጋር ይጀምሩ! ይህ ባለ ሙሉ ቀለም የመማሪያ መጽሐፍ ከ፪ እስከ ፬ (2-4) ዓመት ለሆኑ፣ በተለየ ሁኔታ የተዘጋጀ ቢሆንም ለታዳጊ ሕፃናት፣ ትናንሽ ልጆች፣ አዋቂዎች፣ ከአገር ውጪ ለሚኖሩ የሐበሻ ዲያስፖራ ቤተሰቦች እና ለአማርኛ፣ ግዕዝ እና ኢትዮጵያዊ ለሆነ አጠቃላይ ዕውቀት ፍላጎት ላላቸው በማንኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የተዘጋጀ ድንቅ መማሪያ ነው። በቀን መቁጠሪያዎች፣ በሃይማኖታዊ የእጅ ጽሑፎች እና በባሕላዊ ወጎች ውስጥ ለዘመናት ጥቅም ላይ የዋለውን የተሟላውን የኢትዮጵያ የግዕዝ ፊደላት እና የቁጥር ሥርዓት በጥንቃቄ ያስተምራል። እያንዳንዱ ገጽ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ነፍስ ያላቸው እስኪመስል ድረስ አጉልቶ እና አሳምሮ ለዕይታ ያቀርባቸዋል፡፡ ለተግባራዊ ልምምድ የሚሆኑ ሰንጠረዦች በቀላሉ ለመረዳት ያመች ዘንድ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ መግለጫዎች እና መመሪያዎች አዋቂዎች ልጆቻቸውን ወይም ታናናሾቻቸውን እያስጠኑ ለራሳቸውም የሚሆኑ ዕውቀት የሚገበዩባቸው አጠቃላይ ዕውቀቶች ይህ መጽሃፍ ለመማሪያነት ብቻ ሳይሆን ለመዝናኛነትም እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ በስጦታም መልክ ለሌሎች ቢያበረክቱት የማያውቁትን ከማሳወቅ ባሻገር ግዕዝን እና ኢትዮጵያን ሌሎችን ከማስተዋወቅ አንጻር ለሚያበረክቱት አስተዋጽዖ ይኮሩበታል፡፡ ታዳጊዎች የቅድመ ቁጥር ክህሎቶችን እያዳበሩ ባህላዊ ኩራትን ይገነባሉ፤ ትልልቅ ልጆች እና አዋቂ ጀማሪዎች ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ አጠቃላይ እና አስደናቂ ግንዛቤዎችን ጨምሮ ስለግዕዝ ሆሄያት (ፊደላት) እና ቁጥሮች ጠንካራ መሠረት እንዲያገኙ ለሚከተሉት ሁሉ እንዲስማማ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከቅይጥ ዘር የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን (ሃበሾች) እና ተጨማሪ ቋንቋ ተናጋሪ ልጆችን የሚያሳድጉ የሃበሻ ቤተሰቦች፤ ከ ከ፪ እስከ ፬ (2 - 4) ዓመት ዕድሜ የሚገኙ እና በዓዋቂዎች ክትትል ሥር የሚገኙ፣ ትምሕርት ያልጀመሩ ሕፃናት፤ በማንኛውም ዕድሜ ላይ የሚገኙ የአማርኛ እና የግዕዝ ቋንቋ ወይም ኢትዮጲያዊ ትውፊት አፍቃሪዎች ""ጥንታዊት የሰው ዘር መገኛ"" በመባል የምትታወቀውን ኢትዮጵያ በስነ-ጽሁፋዊ ዓለም የበለጠ ለመረዳት እና ለመቃኘት የሚጓጓ ማንኛውም ሰው ይህ የመጀመሪያ ደረጃ የመማሪያ መጽሃፍ ነው፡፡ ከፍ ባሉ ደረጃዎች እስከምንገናኝ ድረስ የኢትዮጵያዊያንን ስነ-ጽሁፍ እና ስነ-ስሌት መሠረታዊ ባሕሪይ ለመረዳት ወደ ትክክለኛው መንገድ መጥተዋልና እንኳን ደስ አለዎት! በትክክለኛው Full Product DetailsAuthor: Nigussie BerhanuPublisher: Independently Published Imprint: Independently Published Dimensions: Width: 21.60cm , Height: 0.50cm , Length: 27.90cm Weight: 0.227kg ISBN: 9798242590755Pages: 88 Publication Date: 14 January 2026 Audience: General/trade , General Format: Paperback Publisher's Status: Active Availability: Available To Order We have confirmation that this item is in stock with the supplier. It will be ordered in for you and dispatched immediately. Table of ContentsReviewsAuthor InformationTab Content 6Author Website:Countries AvailableAll regions |
||||