|
|
|||
|
||||
Overview"ይህ መጽሐፍ ""ቅን መሪ"" የሚለው መጽሐፍ ተከታይ ነው የመሪ ስኬታማነት መልካም ጠባይ ከችሎታ ጋር ሲደመር ነው (Character + Capacity= Effective Leader) በሚለው እሳቤ ""ቅን መሪ"" የሚለው ስለ መሪ ጠባዕያት የሚዳስስ ሲሆን ባለ ራእይ መሪ (አምስቱ የስኬታማ መሪነት ምሥጢራት) የሚለው ደግሞ የመሪ ችሎታን ይመለከታል ""ባለ ራእይ መሪ"" አምስቱን የስኬታማ መሪነት ምሥጢራት ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በሰፊው ይዳስሳል የስኬታማ መሪነት ችሎታ በአምስት አምዶች ላይ የሚቆሙ ናቸው የሚል እሳቤን የያዘ ነው የመጀመሪያው ባለ ራእይነት ሲሆን ሕልም ማለምን፤ አርቆ ማሰብን፤ አሻግሮ ማዬትን፤ አቅጣጫ ማሳዬትን፤ እንዲሁም በስሌት መምራትን ያካትታል ሁለተኛው ሕልምን ለማሳካት ለውጥን በስኬት መምራት እንዲሁም ለውጥን ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው የሚለውን ይተነትናል ሦስተኛው የስኬታማነት ምሥጢር ከመወሰን ዓቅም ጋር ይያዛል አራተኛው ጠንካራ ቡድን የመገንባትና የማስተባበር እንዲሁም የማስተሳሰር ችሎታ በሌለበት ስኬት አይኖርም የሚለው ነው የመጨረሻው መሪነት ማለት ተከታይ ማፍራትና ለስኬት ማብቃት ነውና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለስኬታማነት ወሳኝ ነው የሚለውን ይመለከታል መጽሐፉ ትኩረት የሚያደርገው በዓቅም ግንባታ ላይ ነውና በሥልጣን ወንበር ላይ ለተቀመጡት ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ቤተሰብን ከመምራት ጀምሮ የተሻለ ዓቅምን ለመገንባት ጥረት ለሚያደርጉ ሰዎች እንዲጠቅም ታስቦ ነው የተዘጋጀው ሕይወትን ለመምራት የሚያስችሉ ቁምነገሮችንም ይቀስሙበታል ሕልም የሌለው ማን አለ? ለውጥ የማይነካውስ? ትልቅም ይሁን ትንሽ ውሳኔ መወሰንም የየዕለት ተግባር ነው ከሰው ጋር ተግባብቶ ለመሥራት ይሁን በሰላም ለመኖር በሰፊው የሚዳሰስበት በመሆኑም ብዙ ማትረፍ ይቻላል ተማሪዎችም ተመራማሪዎችም ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል እምነትም አለኝ" Full Product DetailsAuthor: Tizazuይህ መጽሐፍ ቅን KassaPublisher: Independently Published Imprint: Independently Published Dimensions: Width: 15.20cm , Height: 1.90cm , Length: 22.90cm Weight: 0.472kg ISBN: 9798501032484Pages: 354 Publication Date: 09 May 2021 Audience: General/trade , General Format: Paperback Publisher's Status: Active Availability: In stock We have confirmation that this item is in stock with the supplier. It will be ordered in for you and dispatched immediately. Table of ContentsReviewsAuthor InformationTab Content 6Author Website:Countries AvailableAll regions |